Readers

Your access to and use of the Service is conditioned on your acceptance of and compliance with these Terms.These Terms apply to all visitors, users and others who access or use the Service.By accessing or using the Service you agree to be bound by these Terms. If you disagree with any part of the terms then you may not access the Service Read MoreBy: Oumar Ibrahim

oumar20171@yahoo.com

የኦሮሞ ህዝብ የትጥቅ ትግል ቅንቅኖች

እንደ ኦነግ የከሸፈ ድርጅት የለም። ይህ የትጥቅ ትግል ድርጅት የከሸፈው በመሪዎቹ የተነሳ እንጂ አንግቦ በተነሳው የመገንጠል አቋሙ አይደለም። መሪዎቹ ከአንድ ቀዬ፣ወንዝ፣አካባቢ ወይም ክፍለ ሀገር የመጡ ናቸው። በአጭሩ የወለጋ ክፍለ ሀገር የጰንጤ ኃይማኖት ተከታዮች ናቸው። የኃይማኖቱ ተከታይ መሆናቸው ችግር የለውም። ችግሩ ከነሱ ውጭ ሌላው ኦሮሞ የድርጅቱ መሪ ወይም ቁልፍ ቦታ እንድይዝ አይፈቀድም። ዮሐንስ በንቲ ( ጋላሳ ድልቦ)፣ ዮሐንስ ላታ (ለንጮ ላታ)፣ አብርሐም ላታ ፣ ዱጋሳ ባካኮ ፣ ፍሬው ማሾ ( ዳውድ ኢብሳ)፣ ታደሰ ኤባ…ወዘተ የድርጅቱ እንቀሳቃሾች ናቸው። ይህ ውሸት ነው ብለው የሚከራከሩ አሉ። ይህን ዕውነታ ማየት የማይችል ሰው ዐይን ሳይሆን መስኮት ነው ያለው።


የሌላ ክፍለ ሀገር ኣሮሞዎች ከታችኛው መደርደርያ ስንሆን እነሱ ግን ከላይኛው መደርደርያ ናቸው። የሌላ ክፍለ ሀገር የኦሮሞ ልጆች የድርጅቱ መሪ ለመሆን ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ማሽሎክ ያህል ይከብዳቸዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። በአንድ ወቅት ኦቦ ዮኃንስ ናጋዎ (ዲማ ናጋዎ) የኢሉ አባ ቦራ ኦሮሞ የሆነ፥ የድርጅቱ መሪ ሆኖ ነበር። እሱም የቄስ ጉዲናን ልጅ ባል ስለ ነበር ዕድሉን አገኘ። እሱም ስኮላር ሽፕ ስላገኘ፥ የመሪነቱን ሥራ ትቶ ሴነጋል ለመማር ሄደ። የሚገርም ነው። የእስልምና፣ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን እና ዋቄፈታ ኃይማኖት ተከታዮች ኦሮሞዎች የድርጅቱ የመሪነት ቦታ አይፈቀድላቸውም። ያልተፃፈ የውስጥ ደንብና መማርያ አለ። ለዚህም ነው ጋልጋሎ ከቦራና፣አብደላ ከባሌ፣ ናጋዎ ከአርሲ፣ ሙሜ ከሀራርጌ፣ ላሜሳ ከሸዋ፣ አባ ቡልጉ ከኢሉ አባ ቦራ፣ ዲንሳ ከጎጃምና ይማም ከወሎ ላለፉት 40 ገደማ የመሪነቱን ቦታ የተነፈጉት። ሀምቢሳ ብቻ ድርጅቱን ከእርባ ዓመት በላይ ተቆጣጠረው ማለት ነው። ይህን ዓመት ሙሉ ድርጅቱን ሲመሩ ሞት ይቅርና እሾህ ሟጭሯቸው አያውቅም። ዶክተር መረራ እንዳሉት ” እነሱ ናቸው ወይስ ጥይት ነው ወደ እነሱ የማይሄድው? ” ያሉት። እውነታቸውን ነው የሀረርጌ ፣ የባሌ፣ የአርሲ ፣ ቦረና የሸዋው ኦሮሞው ሲሞት እነሱ ጥብ ለብቻቸው ያላቸው ይመስል አይሞቱም። በደቡብ አፍሪካ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ ሀገራት የምንኖር የሌላ ክፍለ ሀገር የኦሮሞ ልጆች የኮሚኒቲ መሪ እንኳ እንዳንሆንና እንዳንደራጅ ጋሬጣ እየሆኑብን ነው። ውጭ አገር ሆነህ ስብሰባ ላይ ጥያቄ ብትጠይቅ ወይም ብትተቻቸው ቁጭ በል ትባልና ትቀመጣለህ። ከዛ ከስብሰባው ስትወጣ ስምንህን ጥላሸት ይቀባሉ። ኦሮሞም አይደልህም ተብሎ ይወራበሀል። ያገሉሀልም። ኦሮሞነትንም የተባበሩት መንግሥታት ስንዴ ይመስል ሲፈልጉ ይሰጡኃል ሲያሻቸው ይነፍጉኃል። የሚገርመው ደግሞ አንዳንዶቹ አባታቸውን እንኋ አያውቁም። እንደ በንጂ አራዳችን የበቀሉ ናቸው። አባታቸውን አለማወቃቸው ችግር የለውም። ችግሩ ከኦሮሞ አባትና እናት ተወልዶ፥ አፋን ኦሮሞ እየቻለ፥ ጫካ ገብቶ ታግሎ፥ ወንድሙንና እህቱንም ጭምር ያጣውን ሰው እንዲህ ማለታቸው ያናድዳል። አገር ቤት፥ ሱዳን፥ኬንያና ዩጋንዳ ሆነህ የድርጅቱን አመራር ከተቸህ ትገደላለህ። ወይም ደግሞ ለጠላት ምስጢር በማውጣት ያስገድሉኃል። የድርጅቱ ልብ ሆሮጉዱሩ ፥ ፔንጤ – ፔንጤ – ጴንጤ ይላል። አካሉ ደግሞ ኦሮሞ – ኦሮሞ – ኦሮሞ ይላል። አካሉና ልቡ አልተጣጣሙም። እኛ ኦሮሞ አይሉንም። ሴቶቻችንን ነው ኦሮሞ የሚሉት። እኛ የምንፈለገው ለእግረኛ ጦር ጫካ በነበሩበት ወቅትና ገንዘብ ለማዋጣት ብቻ ነው።


የሚገርመው ደግሞ ፥ ድርጅቱን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ድርጅት ወደ ፊት እንዳይሄድ ሆን ብለው አኮላሹት። ዮኃንስ ላታ በወቅቱ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ የነበረው በእሳያስ አፈወርቂ አማካሪነት የኦነግን ጦር ሰብስቦ እንደ ከብት በረት አጎራቸው። ከዛም በሻብያና በወያኔ ውታደሮችች እንዲከበብ አስደረጉት። በዚህም በረት ውስጥ ብዙዎቹ በድብደባ፣ በተስቦ በሽታና ወባ እንድያልቁ ተድርገዋል። ሽሹ እንክዋን አላላቸውም። እሱ ግን የኢትዮጵያ ፓስፖርት ተሰጥቶት፣ የገንዘብ ድጎማ ተደርጎለት የኦሮሞን ህዝብ አደራ ሽጦ የፈረጠጠ ከንቱና ሆደ አምላኩ ሰው ነው። አቶ መለስ ዜናዊ ዮኃንስ ላታ ቀደም በሚስዮናውያን ትምህርት ቤት ውኔውን እንተዘረፈ፥ በውጊያ የማያምንና የዞረበት እንደሆነ ያውቀው ነበር። ዮኃንስ ላታ “ሌንጮ” የሚል ተራራ የሚያክል ስም ይዞ የሚዞር እንጂ ቀፎ መሆኑን በሚገባ ያውቅ ነበር። ለዚህም ነበር ስያስፈልገው አገር ቤት እያስመጣ ፥ አንዳንዴም በአውሮፓና በአሜሪካ መዲናዎች በእምባሲ ተወካዮች አማካኝነት ያማልለው ነበር። ሌንጮም አቶ መለስ ጋር እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ግንኙነት እንደ ነበራቸው ተናግረዋል። ዶክተር መረራ እንዳሉት “የኦሮሞ ህዝብ እንግደ ልጅ” ያሉት እውነት ነው። ኦቦ ሌንጮ ለትግሬዎች ሽጦን ወደ ካናዳ ከተመ። በኋላም በማናውቀው ምክንያት ካናዳን ትቶ ኖርወይ መኖር ጀመር። ትያትሩ ግን አሁንም እንደ ቀጠለ ነው። በምን ያህል ዋጋ እንደምንሸጥ እንጃ እንጂ ኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፍሮንት የሚባል ድርጅት አቋቁሞ እያስማማን መሆኑ ግልፅ ነው። ይህ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል የሚለውን አቋም ኦነግ ውስጥ እያለ በድብቅ ስያራምደው የነበረ ሲሆን፥ ኦነግ ጫካ በነበረበት፥ የበታች አዋጊ የነበሩት እነ ኦቦ ናዲ ጋማዳ የመሰሉ ጀግኖች በጠላት እንድያዙ ውይም እንዲሞቱ የተደረገው ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነበር።


ኦነግ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1991 ከሽግግስሩ መንግሥት ከወጣ በኋላ አስመራ ጥገኝነት ጠይቆ እዛው ገባ። በጣም የሚገርመው ኦነግን ያሽመደመደውን አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ደግመው ማመናቸው ነበር ያስገረመን። ለምን ሲባሉ ቋሚ ጥቅም እንጂ ዘላለማዊ ጠላት የለም ይሉናል። ይቺ አባባል በፖለትካል ሳይንስ ትዘወተራለች። እኔ ግን አትመቸኝም። ግን አንዳንዴ ዘላለማዊ ጠላትም አለ። የኤርትራ መንግሥት ትላንትም ዛሬም ነገም የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የፈረጠመ የፖለትካ ኃይል እንዲሆን አይሻም።


ኦነግ አስመራ እያለ አቶ ፍሬው ማሾ ኦቦ ጋላሳን በጠረባ ጥሎት ድርጅቱን ይቆጣጠራል። ኦቦ ጋላሳ ከሌሎቹ በጣም ይሻል ነበር። ግን ተፈንግሎ ቀረ። ከዛም ድርጅቱ ለሁለት ይከፈላል። የፍሬው ማሾ ሸኔ ፥በኦቦ ጋላሳ የሚመራው ደግሞ ቃማ ጨሁምሳ በመባል ይታወቃል። የቃማ ጨሁምሳ መሪ ለንደን፣ እንግልዝ አገር ገባ። ድርጅቱም ከኦሮሞ ህዝብ በመራቁ ደበዛው ጠፋ። አቶ ፍሬው የኦነግ መሪ ሆነው ከተቸከሉ በኋላ ኦነግ ከጥቂት የጴንጤ ኃይማኖት የወለጋ ኦሮሞውዎች እጅ ወጥቶ መቶ በመቶ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሆነ። እንደ ኦፒዲኦ ኦነግም አፋን ኦሮሞ መናገር በሚችሉት ባዳዎች ታጭቋል። ችግሩ ኦሮሞ አለመሆናቸው ሳይሆን ኦሮሞ ነን እያሉ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ደባ መስራታቸውና የባርነት ሠንሠለት ከሚገምዱት ጋር መቧድናቸው ነው።


አቶ ፍሬው ማሾ በደርግ መንግሥት፥ በወለጋ ክፍለ ሀገር የአሥራ አንድ የኦነግ አባላት መሪ ሆኖ መርዝ በልተው እሱ ሳይሞት ሌሎቹ አለቁ። ለምን? የሚያጠያይቅ ጉዳይ ነው። ከዛም ታሠረ። ክጥቂት ዓመትእሥራት በኋላ አመለጠ ተባለ። ምን ይሄ ብቻ አሁን “ቄሮ” የሚባል ድርጅት አቋቁሞ እውነተኛውን ቄሮ እየናደ ነው። በዋሽንግተን ዲሲ አለማቀፍ የቄሮ ድርጅት ብለው ሌላ ተለጣፊ ድርጅት አቋቁመው ብቅ አሉ። በአገር ቤትም ተለጣፊ ቄሮ አላቸው። በውጭ አገር ከሚኖሩት የኦሮሞ ልጆች የተሰበሰበውን የቄሮ መርጃ ገንዘብ ለግላቸው ጥቅምና ለቄሮ መናጃ አርገው እርፍ አሉ። ይህን ዓለማቀፍ የቄሮ ድርጅት ዲሲ፣አሜሪካ ሆነው የሚመሩት ስድስት ሰዎች ናቸው ይባላል። ዝርዝር ስማቸው ወደ ፊት ይገለፃል። እነዚህ ሰዎች የአስመራው ኦነግ (ሸኔ) አባላት ሲሆኑ ስድስቱም የሆሮ ጉዱሩ ጉዶች ናቸው። ለምን ቢባል ከነሱ ኦነግ ውጭ የኦሮሞ ድርጅት አይሎ ከወጣ የነሱ ድርጅት መጥፍያው ነውና። የኦሮሞ ህዝብ ለዘላለም ባርያ ሆኖ መኖር አለበት የሚለውም የኤርትራ መንግስሥት አቋምም ሲለሚከስም ነው። የኤርትራ አሽከርም የሆኑት እነሱን የሚቃወሙትን ኦሮሞች ብቻቸውን ሆነው ማሸነፍ ስለሚሳናቸው፥ በኤርትራ እየታገዙ ለመኮርከም ስለሚያመቻቸው ነው። በዛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራን ጥቅም ለመጠበቅ ነው።


አቶ ፍሬው የዩትዩብ ጀግና ነው። በዩትዩብ የኦሮሞ ብልሱማ ያስፈልገዋል ፤ኦሮሞ ተጨቁኗል ማለት አይሰለቸውም። ምክንያቱም በውጭ አገር የሚኖሩትን ኦሮሞዎች ለማማለልና ከደቡብ አፍሪካ፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳና ከአውሮፖ አገራት ለኦሮሞ የጀግኖች ቀንና ለኦነግ ተዋጊዎች እየተባለ የሚስሠበሠበው ገንዘብ ምንጩ እንደዳይደርቅበት ነው። በዩትዩብ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ድምፅ ወይም በሳጋለ ብልሱማ ውሸቱን ይነዛል። በየጊዜው 70፣15፣100 …ወዘተ የጠላት ወታደሮችን ገደልን እያለ ይዋሸናል። ይህንን ሬድዮ ጣቢያ የሚዘውሩት ኤርትራውን ናቸው። ይህ ድርጅት አስመራ ተወሽቆ ገደልኩ የሚለው ቢቆጠር የወያኔ ጦር ግማሹ ሞቷል ማለት ነው። በአንዳንድ የኦሮሞ ድህረ ገፆች(ወብሳይቶች) የዚህን ሰውዬ እንደ መጫኛ አንዳንዴ እንደ ዓባይ ወንዝ የረዛዘሙ ዓረፍተ ነገሮችን የያዛ መግለጫዎችን ብዙ ጊዜ ይለጥፋሉ። ይህም ብዙ በውጭ አገር የሚኖሩትን ኦሮሞዎች ቀልብ ለመሳብ ነው። ነገር ግን የዚህን ሰውዬ ማንነት በውጉ የሚያውቁ አይመስለኝም።ይህ በኢሳያስ ሳንባ የሚተነፍሰው የፍሬው ማሾ ድርጅት የበሬ ግንባር የምታክል ኩርማ መሬት/አራዳ ለአምስት ደቂቃ ነፃ አውጥቶ አያውቅም። ተመኝቶም አያውቅም። ምክንያቱም ዓላማው እይደለምና። ዓላማው የኦሮሞን ህዝብ መከፋፈልና መናድ ነው። ከተቻለ በሻብያ ታጅቦ ኦሮሞ ነኝ እያለ አፋን ኦሮሞ እየተናገረ ሥልጣ ላይ ቁብ ለማለትና የትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ለመጠበቅ ነው። ከኦሮሞ ህዝብ የወጣ እውነተኛው ቄሮ እያለ ሌላ ቄሮ መመሥረት ለምን አስፈለገ? እውነት ለኦሮሞ ህዝብ የሚቆረቆር ቢሆን ኖሮ ነባሩን ቄሮ እሮምሱ (ማጦንቸት) እንጂ ሌላ ተለጣፊ ቄሮ ባልተቋቋመ ነበር። ይህ ድርጅት ማንም የኦሮሞ ድርጅት ከሱ እንዲበልጥ አይፈልግም። በአስመራ ከተማ ጣሊያን በሰራው ቪላ ውስጥ ተወሽቆ ቢሉሱማ ቢሊሱማ እያለ ይሸልላል። እሱን ብሎ ነፃ አውጪ። አንተ ከኛ አይደለህም። ምክንያቱም ለኦሮሞ ህዝብ ውድቀት ጉድጓድ እየቆፈርክ ነው። የባርነት ሰንሰለትም እየገመድክ ነውና።


በግምት አንድ ወር ይሆናል። አቶ ፍሬው ማሾ እነ ቸጉ ቬራ የለበሱትን የወታደር ዩኒፎርም ለብሶ በአያንቱ ድህረ ገፅ ጉብ ብሎ አይሁት። ያ ዩንፎርም ትርጉሙን ብያውቅ አይለብሰውም ነበር። መቸም ኦሮሚያ ሂዶ እንደማይዋጋ አውቃልሁ። ኦሮሚያን ነፃ እናወጣለን ብለው ኤርትራ ይሄዱትን የኦሮሞ ወጣቶች ለመንገድ ሥራ፥ አረም ለማረም፥ ዕፅዋት የናፈቀውን የኤርትራ ተራሮች ለማልማትና ችግኝ ለመትከል ካልሆነ በሥተቀር ምንም እንደማይሠሩ አውቃለሁ። ከዛ አምልጠው የመጡት ነግረውናል። እርግጥ ነው ኤርትራ ማለት ቤርሙዳ ነው። መውጫ የለህም። ሆነም ቀረ ትግል ከህዝብ መሀል በመሆን የሚደረግ ነው። አንድ ድርጅት ከህዝብ ከተለየ ህይወት የለውም። በድን ነው። ሬሳ ነው። ህዝብ በሰው አካል ይመሰላል። መሪ ደግሞ በነፍስ። መሪና ህዝብ ከተለያየ ያ ድርጅቱ አከተመለት ማለት ነው። ከባህር የወጣ አሳ። ኦነግም ከኦሮሞ ህዝብ ወጣና ነብሱ ወጣ። አቶ ፍሬው ማሾም ከአስመራ ማጀት ሆኖ ከመርመጥመጥ በስተቀር ምንም ሥራ አልሰራም። ከሀያ ዓመት በላይ አስመራ ኖሯል። አንድ ቀን እንኳ ሳያዋጋ ዓመቱ ነጎደ። መሸ። ለነገሩ አነሳሁት እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ነፃ ማውጣት በሱ መዝገበ ቃላት የለም። ፍሬው በአካልም በመንፈስም ኤርትራዊ ነው።አቶ ፍሬው ‘ዳውድ’ የተባለውን የጫካ ስም ያወጡለት እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ንጉስ ዳውድ ጀግና ይሆናል ብለው ነው። ጀግነት በስም ይጋባል እንዴ? ጉድ ነው። ንጉስ ዳውድ በቡጢ አንበሳ ገድሏል ይባላል። ይኸኛው ዳውድ ከአስመራ ማጀት ሲንደፋደፍ እንጂ የሽምቅ ተዋጊ ጦር መርቶ ጠላት ሲደመስስና የእጅ መዳፍ የምታክል መሬት ነፃ ሲያወጣ አላየንም።


ኦነግ እንደ አውርፖ አቆጣጠር በ1967 ዓ.ም በሞቃዲሹ፣ ሱማሊያ ተቋቋመ። ያቋቋሙትም እነ ሻንታም ሹቢሳ፣ ጃራ አባ ጋዳ፣ ሁሴን ሶራ፣ ሉጎና ሌሎች ሰዎች ናቸው። የድርጅቱም ባንዲራም እዛው ነው የተቀረፀለት። ተዋጊም ኢራቅ፣ሲርያና የመን ተልከው እንዲሰለጥኑ ተደርጓል። ወደ አገር ቤትም ተመልሰው ከጠላት ጋር ተፋልመዋል። በዚህም ጦርነት ብዙ ኦሮሞዎች ተሰውተዋል። ኤሌሞ ቅልጡም ከተሰዉት ውስጥ ከሚጠቀሱት አንዱ ነበሩ። ይህንን ድርጅት ነው የሆሮ ጉዱሩ ኦሮሞች ናቸው ያቋቋምነው ብለው የሚከራከሩት። ተጠለሉበት እንጂ አላቋቋሙትም። ለነገሩ አነሳሁት እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ትኩረት ወያኔን በመገንደስ ላይ መሆን አለበት።


በደርግ መንግሥት ጊዜ ደርግን ሲቃወሙ ከነበሩት ውስጥ መ.ኢ.ሶንና ኢ.ጭ.አ.ት ይገኙበታል። ደርግ ስያሯሩጣቸውና መግቢያ ስያጡ ሀረርጌ ሄደው ኦነግን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1976 ዓ. ም ይቀላቀላሉ። እነ ኦቦጃራ አባ ጋዳም ኦሮሞን ሁሉ በትግሉ መስክ ለማሳተፍ ጥሩ እድል ብለው በደስታ ተቀበሏቸው። ብዙም ሳይቆይ ድርጅቱ በነዚህ ሰዎች መናጥ ጀመር። የጥቂት ጴንጤዎች ክለብ አርገው እርፍ አሉ። ድርጅቱ የኦሮሞነት ውብትና ለዛ ራቀው።ኦሮሞ ኦሮሞ መሽተቱ ቀርቶ ጥቂት የወለጋ ጴንጤ – ጴንጤ መሽተት ጀመር። ኦሮሞ በጣም ውብ የሆነ የመተዳደርያ ሥርዓትም አለው ይሉናል ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ አንድ ቀን ይህንን ሥርዓት ሳይተገብሩት ከአርባ ዓመት በላይ ሆ ናቸው። ድርጅቱ ጤና አጣ። ነቀርሳ አካሉን ነዳደለው።ለከርሰ መቃብርም አበቁት። ድርጅቱን ያቋቋሙት ከድርጅቱ እየተገፉ ወጡ። ሂድ አትበለው እንድሄድ አርገው ይባል የለ። ሙሉ በሙሉ ድርጅቱን ከተቆጣጠሩትበኋላ፥ ድርጅቱን ያቋቋምነው እኛ ብለው የሌለ ታሪክ መጻፍጀመሩ። የዘመናችን ጉደኞች ናቸው።


ይህ ድርጅት ማዕከላዊነት አሰራርም የጎደለውና ተጠያቂነትም የለውም። ኦቦ ሌንጮ ይህን ያህል ሲያቦካ ማን ጠየቀው? በአንድ ወቅት አንድ የኦሮሞ ምሁር ሻቢያ ጫካ በነበረበት የመጎብኘት ዕድል አግኝተው ነበር። ሻቢያ ጫካ ሆኖ መንግሥት ይመስላል አሉ። አሰራራቸው፥ የሥራ ክፍፍላችው በጣም የሚገርም ነው አሉ። ወያኔንም ለመጎብኘትም ጎራ ብለው ነበር። ይሄም አሠራራቸው ከሻቢያ ትንሽ ይነስ እንጂ ድንቅ ነበር አሉ። ውደኛው ኦነግ ሲመጡ ግን ባዶ መሆኑን አይተው በጣም ተገረሙ። እውነት ነው ፥ኦነግ የድርጅት ይዘትና መልክ የለውም። ሻቢያና ወያኔ ጎበዝ መሪዎች ስለ ነበሩዋቸው ፥ በውጊያ ስለሚያንኑ፥ የምዕራቡን ዓለም ድጋፍ መጠቀም በመቻላቸው፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና ስላገሸገሸውና ደርግም ከከፍተኛ ባለ ሥልጣኔች ጋር ቅራኔ ውስጥ በመግባቱ ዕድሉን ትተጠቀሙና ድርግን እሸነፉ። የኛዎቹ ግን ቦቅባቃዎች ናቸው። ፈረንጆች ፈሪ ጎዳንሳ የለውም ይሉ የለ።
የኦሮሞ ህዝብ፥ከነዚህ የትጥቅ ትግል ቅንቅኖች፣ ደዌዎች፣አረማሞዎች፣ ነቀርሳዎች፣ ነቀዞች፣ ብሎችና ኦርታዎች አንዳች ነገር መጠበቅ የለበትም። እነዚህ የባርነትን ሰንሰለት የሚገምዱ እንጂ የሚጎምዱ አይደሉም። ለምን አትዋጉም ብለን ስንጠይቃቸው ወደብ የለንም፣ብዙ የተለያንዩ ብሔረሰቦች ኦሮሞ መሀል ይኖራሉ፣ የዓለም ፖለትካ ተቀይሯል፣ ጥሩ ጎረቤት አገራት የሉንምና መሳሪያ የለንም እያሉ ተልካሻ ምክንያቶችን ይደረድራሉ። ሺ የሰጠ አጋጣሚዎች ተፈጥረው አንዱንም ሳይጠቀሙ ቅሌን ጨርቄን ሲሉ መሸ። ከሽግግር መንግሥቱ እንኳ ከወጡ ሩብ ምዕተ ዓለም አለፈ። አንድ ቆራጥ መሪ ቢኖረን ኖሮ፥አገራችንን መጋዣ የዋለበት እርሻ ያስመሰሉትን የትግራይ ጌሪዎች በድንጋይና በሽመል ወደ መጡበት ጉራንጉር መመለስ ይቻል ነበር። አብዲሳ አጋና አቢሼ ጋርባን ያፈራ ምድር እነዚህን ጨገጎቶች ማፍራቱ ይገርማል። ከራያ አዘቦ እስከ ሞያሌ ፥ከቄለም እስከ ዋጫለ ሶማሊያ ድንበር ያለውን ሰፊ የኦሮሞ ህዝብና ገዢ መሬት ተጠቅመው ለህዝባቸው ፉይዳ ማምጣት ተስኗቸው ይጃጃላሉ።


በአጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ በኢሳያስ አፈወርቂ ሳንባ ከሚተነፍስ ኦነግ ምንም መጠበቅ የለበትም። በሰላማዊ መንገድ የሚደረገው የቄሮ ትግል እንዳለ ሆኖ፥ አገር ቤት ያለችውን ኦነግ ጠጋግናችሁ ከአገር ቤት መሪ ኖሮት፥ መሪው የደፈረሰ ውኃ እየጠጣ፥ ድንጋይ እየተንተራሰ፥ የመንግሥት ባንክ እየዘረፈ፥ከጠላት ትጥቅ እያስፈታ ወደ ፊት የሚገሰግስ ኦሮሞ የሆነ፥ ቆራጥ መሪ ያስፈልጋችሀል። ወያኔ የኦሮሞ ወጣቶች፣ባልቴቶች ሽማግሌዎች፣እርጉዞችና ህፃናት በጥይት ሲቆላ የኦነግ ‘መሪ’ ከስመራ መዲና ከመሸለል በስተቀር አንድ ወያኔ መግደል አልቻለም። አላማውም አይደለም። ወያኔ የኦነግን መሪዎች በጣም ትወዳቸዋለች። ምክንያቱም ኦሮሞ ጎርፍ ነው ። ይህንን ጎርፍ ጠላት ለመናድ አልተጠቀሙበትም። እግዚአብሄርም የማቱሳላን እድሜ እንዲቸራቸው ፀሎት እያደረገች ነው። በኦሮሞ ህዝብ ደም እየነገዱ ነው። ኦነግ ከነዚህ አጋሰሶች እጅ ውቶ የኦሮሞ ህዝብ አካል መሆን አለበት። ወያኔ በነዚህ ደዌዎች ድክመት የተነሳ ነው የኦሮሞን ህዝብ እየገዘገዘች ያለችው። የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ላይ የተጠመጠውን እባብ መግደል የሚችለው ራሱ ነው። ከነዚህ ውጭ አገር ከሚኖሩ ጉቶዎ ነፃነት መጠበቅ የለበትም። አስመራ ፔርሙዳ ነች። ከአስመራ ባርነት እንጁ ነፃነት አይመጣም። ነፃ የሚያወጣህ እዛው አገር ቤት ያለው ኦሮሞ ነው። በፊትም እነዚህ አስመሳዮች ነበሩ፥ በአስመራ አማካሪነት፥ ሻቢያን አምነው ወያኔ አገራችንን እንደ አንበጣ መንጋ ያስወረሩን። ኦሮሞ ንቃ! ንቃ! ንቃ!

ዑመር ሁሴን
5/27/2016

 

 


The views and opinions expressed on this web site are solely those of the original authors and other contributors. These views and opinions do not necessarily reflect the Furdanews.com staff and its management.